ከ48 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ታዳጊዎች የተሳተፉበት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ማጠቃለያ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂድዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2017
የዓድዋ ድል መታሰቢያ
ከ48 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ታዳጊዎች የተሳተፉበት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ማጠቃለያ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂድዋል።
የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድሩ በአብርሖት ቤተ-መጽሀፍት እና የአፍሪካ ሲልከን ቫሊ ትብብር “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለበጎ ተጽዕኖ” በሚል መሪ ሃሳብ ሲያካሄድ ቆይቷል።
በዛሬው እለት ደግሞ የማጠቃለያ ስነ ስርአቱ በአድዋ ድል መታሰቢያ ተካሄድዋል።
ከግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ግዙፍ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ውድድር ከ48 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 4 ሺህ 928 ታዳጊ ወጣቶች ተወዳድረውበታል።
በትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና እና በመሳሰሉት ወሳኝ የፈጠራ ስራዎች ለችግሮች መፍትሄ የሚሆኑና ቀልጣፋ አሰራር የሚፈጥሩ ፈጠራዎቻቸውም ለውድድር ቀርበዋል።
በዚህም አገራቸውን በመወከል ምርጥ ሰባት ውስጥ የገቡ የኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ፣ ታንዛኒያ፣ አልጀሪያ እና ቱኒዚያ ታዳጊዎች ለመጨረሻው ውድድር ቀርበዋል።
በማጠቃለያ መርሃግብሩ የአብርሖት ቤተ-መጽሐፍት እና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ስራ አስኪያጅ ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን አማረ፣ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
//////////////
The biggest final tech competition in Africa, in which the young people from 48 African countries participated was held at the Adwa Victory Memorial.
Addis Ababa, October 16, 2024
Adwa Victory Memorial
The biggest final tech competition in Africa, under the theme “Artificial Intelligence for impact”, which was held by A2SV Hackathon, Addis Ababa’s city Administration and the Adwa Victory Memorial in which the 4928 young people from 48 African countries participated was held at the Adwa Victory Memorial.
The final teams presented their innovations about education, health, agriculture, etc.,
The top seven finalists that represented their countries were from Ethiopia, Ghana, South Africa, Nigeria Tanzania, Algeria and Tunisia.
During this event, Engineer Wubayehu Mamo; director of the Adwa victory memorial and Abrehot library, Solomon Amare; Head of Addis Ababa’s city administration innovation and technology bureau, Mrs. Huria Ali; Minister of women and social affairs, Emre Varol; CEO of A2SV, were present.
Prizes were given to the top 3 team winners. 3rd place being Team Bitbybit from Ethiopia, with a prize of $4000 dollars, 2nd place being Team Harrisa from Tunisia, with a prize of $6000 dollars, and 1st place being Team BEEMO from Tunisia, with a prize of $10,000 dollars.