አዲስ አበባ፤የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም
ከቡታጅራ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ መምህራን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ጉብኝት አካሂደዋል፡፡
መምህራኑም በጉብኝቱ ወቅት በሰጡት አስተያየት የአድዋ ድል ታሪክ በታሪክ መፃህፍት እና በኪነ ጥበባዊ መንገዶች በተለያየ ጊዜ በልዩ ልዩ መልኩ ሲገለፅ የቆየ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ታሪክ ነው ያሉት መምህራኑ ይህ የመታሰቢያ ሙዝየም ግን አኩሪ የድል ታሪካችንን ምስል ከሳች በሆነ መልኩ በማሳየት “የታሪክ ቤተ ሙከራ” ሆኖ አግኝተነዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉ መምህራንም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየሙ በነበራቸው ቆይታ ያገኙትን እውቀት ለተማሪዎቻቸው ለማጋራት ማቀዳቸውንም ጠቁምዋል፡፡