Adwa Victory Memorial

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት በኩል የመጡ የአልጄሪያ ቢዝነስ ዴሊጌሽን አባላት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

March 5, 2024
Adwa Victory

የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምበአልጄሪያ ሀገር ቶፕ የተሰኘ የህክምና የእጅ ጓንት አምራች ኩባንያ የበላይ አመራሮች ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሀገሪቱ መምጣታቸውን ተከትሎ ከዚህ ቀደም በምስል የተመለከቱትን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በአካል ለመጎብኘት በመወሰን ጉብኝቱን ማካሄዳቸውን ገልፀዋል፡፡

የአደዋ 00 ስያሜ ከምን መነሻ ስለመሆኑ የጠየቁት አባላቱ 00 ኪ.ሜ መነሻ ቦታ ፦ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መሐከል ላይ የሚገኘው የኮምፓስ ምልክት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ቦታ በመሆኑ ስያሜውን እንዳገኘ በመታሰቢያ ሙዚየሙ አስጎብኚዎች ምላሽ ለማግኘት ችለዋል፡፡

የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ መሀል ፒያሳ ላይ የተገነባው ግዙፉ የ ” ዓድዋ ድል መታሰቢያ ” በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተመርቆ መከፈቱም ይታወሳል፡፡

Leave a comment

Recent Posts