የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም
በእለቱም የዘንድሮውን የኢጋድ ፓርላማ ተወካዮች አመታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄዱን ተከትሎ ጉብኝት ማካሄዳቸውን የገለፁት አባላቱ ዓድዋ ለኢትዮጵያዊያን እና ለአፍሪካዊያን ድል፤ ለነጭ ወራሪዎች ደግሞ የሰው ልጅ እኩልነት ያስተማረ ታላቅ ታሪክ እንደ መሆኑ መጠን እንዲህ ያለ ታሪክን በግልፅ የሚያሳይ መታሰቢያ ሙዝየም ለእይታ በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት እንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡
በእለቱም በመታሰቢያ ሙዚየሙ ነጋሪት፣ የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያን የተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶችን የጎበኙት አባላቱ በዘመኑ የነበረው የስልጣኔ ደረጃ ግርምት እንዳጫረባቸው ገልፀዋል፡፡
አንድ መቶ ሃያ ሺህ ጀግኖችን የሚዘክር ማስታወሻ፣ የዓድዋ ድል ለፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መነሻ መሆኑን ማሳያነቱን የያዘው መታሰቢያው የየዘመን ድሎችን ለማመላከትም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የሚያሳይ ፋውንቴንም ተሰርቶለታል።